በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ዝርዝር አልተቀየረም


በወቅታዊ ዘገባዎች ላይ የሚተነትኑ ጋዜጦች ለሽያጭ በጎዳና ላይ ዳካር፤ ሴኔጋል እአአ የካቲት 16/2024
በወቅታዊ ዘገባዎች ላይ የሚተነትኑ ጋዜጦች ለሽያጭ በጎዳና ላይ ዳካር፤ ሴኔጋል እአአ የካቲት 16/2024

የሴኔጋል ሕገ መንግሥታዊ ምክር ቤት የተሻሻለውን የፕሬዚደንታዊ ምርጫ እጩዎች ዝርዝር አውጥቷል። 20 እጩዎችን በያዘው ዝርዝር ውስጥ ያልተካተቱት አንዲት እጩ ብቻ ሲሆኑ፣ በገዛ ፈቃዳቸው ከምርጫው ራሳቸውን በማግለላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ራሳቸውን ከምርጫው ያገለሉበትን ምክንያት አልገለጹም፡፡

እኤአ የካቲት 25 ሊደረግ የነበረው ምርጫ በመንግሥት ውሳኔ ላልተወሰነ ቀን የተለላፈ ሲሆን መች እንደሚደረግ አሁንም አልተገለፀም።

ሕገ መንግሥታዊው ምክር ቤት ምርጫው እስከ ታህሣስ ወር እንዲዘገይ የቀረበውን ረቂቅ ህግ ሽሯል፡፡

ምርጫውን የማዘግየቱ ውሳኔ ምዕራብ አፍሪካዊቱን ሀገር ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ውጭ ያደረገ ሲሆን በመንግሥቱ ላይ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

“ምርጫውን ማራዘም ያስፈለገው በእጩዎች ዝርዝር ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ነው” ያሉት ፕሬዚደንት ማኪ ሳል፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብሩ እና በተቻለ ፍጥነት ምርጫውን የሚካሄድበትን ምክክር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

ከዋነኞቹ የፖለቲካ ተቃዋሚ መሪዎች መካከል በእስር ላይ የሚገኙት ኦስማን ሶንኮ እና የቀድሞ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ልጅ ካሪም ዋዴን ጨምሮ ታዋቂ ተቃዋሚዎች በእጩዎች ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG