በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል የምርጫ ጊዜ መራዘሙን ተከትሎ ፖሊስ እና ተቃዋሚዎች ተጋጩ


ፕሬዝዳታዊው ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ተከትሎ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዳካር በተጠሩት ሰልፎች ላይ ተቃውሞዎች ነበሩ፣ ዳካር፤ ሴኔጋል
ፕሬዝዳታዊው ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ተከትሎ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዳካር በተጠሩት ሰልፎች ላይ ተቃውሞዎች ነበሩ፣ ዳካር፤ ሴኔጋል

የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ከሶስት ሳምንታት በኋላ በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ለየካቲት 25 ታቅዶ የነበረው ፕሬዝዳታዊው ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ማስታወቃቸውን ተከትሎ ትናንት እሁድ በዋና ከተማይቱ ዳካር የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊዎች እና ፖሊሶች ተጋጭተዋል፡፡

ይፋ የምርጫ ቅስቀሳው ሊጀመር አንድ ቀን ሲቀረው ፕሬዚዳንት ሳል በብሔራዊ ምክር ቤቱ በህገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት መካከል እጩ ተፎካካሪዎች ከምርጫው እንዲወጡ መደረጋቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ የተነሳ ጣልቃ ለመግባት መወሰናቸውን ይፋ በማድረግ ሀገሪቱን ካልታወቀ ሁኔታ ውስጥ አስገብተዋታል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

የሴኔጋል ፓርላማ አባላት የምርጫ ሂደቱን በተመለከተ የአመኔታ ጥያቄ በተነሳባቸው ሁለት የህገ መንግሥታዊው ምክር ቤት ዳኞች ላይ ምርመራ እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ነጻ፣ ግልጽ እና ሁሉን አቀፍ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ግልጽ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀመር አደርጋለሁ”

“ነጻ፣ ግልጽ እና ሁሉን አቀፍ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ግልጽ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀመር አደርጋለሁ” ያሉት ፕሬዝዳንት ሳል ምርጫውን ስለሚካሄድበት ቀን ግን ያሉት የለም፡፡

አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ያሰሙትን ጥሪ በመቀበል፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንዶች እና ሴቶች የሃገሪቱን ባንዲራ እያውለበለቡ፣ ሌሎችም የብሔራዊ እግር ኳስ ቡድኑን መሊያ ለብሰው፣ በዋና ከተማይቱ አውራ መንገዶችና አደባባዮች ተቃውሟቸውን ለማሰማት መሰባሰባቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የተጠቀሙት ፖሊሶች፡ የሸሹትንም ሲያሳድዱ ታይተዋል። አንዳንድ የተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎችም በበኩላቸው በፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወር ምላሽ ሰጥተዋል።

ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር የተመዘገቡ እጩዎችም የምርጫ ጊዜውን በይፋ መራዘም በመቃወም በመጭው እሁድ ዘመቻቸውን እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG