በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል ምርጫ


በየካቲት 17ቱ የሴኔጋል ምርጫ ፕሬዚዳንት ማኪ ሣሊ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት አስታወቀ።

ሣሊ ለሁለተኛ የሥራ ዘመን እንደገና የተመረጡት ከጠቅላላው ድምፅ 58 ከመቶውን አግኝተው መሆኑንም ፍ/ቤቱ አስረድቷል።

“ሕዝቡ በእኔ ላይ ያለውን እምነት ዳግም ማረጋገጡ በእጥፍ ጠንክሬና በተሻለ እንድሰራ ያበረታታኛል” ብለዋል ማኪ ሣሊ።

ሣሊ ደጋፊዎቻቸውን ያበረታቱ ሲሆን ተቃውሞ ካሰሙ ተፎካካሪዎቻቸው ጋር አንድነት ለመፍጠርም ጥሪ አቅርበዋል።

የሣሊ መንግሥት ሁለት ጥንካራ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት - በምርጫው እንዳይሳተፉ በሙስና ወንጀሎ አሳግዷል ሲሉ - አንዳንድ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ቡድኖች ይተቻሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG