የሴኔጋል ጉምሩክ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ በድምሩ ከ50 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ሦስት የኮኬይን ጭነቶች መያዙን ትላንት ማክሰኞ ዕለት አስታወቀ።
የጉምሩክ ባለስልጣናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአጎራባች ሀገሮች፣ በተለይም በላቲን አሜሪካ እየተመረተ ወደ አውሮፓ የሚጓዘውን አደንዛዥ ዕፅ ማስተላለፊያ ከሆኑት ጊኒ፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ-ቢሳው እና ማሊ የሚገባውን ኮኬይን በብዛት እየያዙ ይገኛሉ።
ፖሊስ ትላንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ከማሊ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ አንድ ማቀዝቀዣ ያለው የጭነት መኪና መያዙን አስታውቋል፡፡
"በድምሩ 306.24 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የያዙ 264 እሽጎችን በማቀዝቀዣው ውስጥ ባለው የአየር ማናፈሻ ክፍል ውስጥ በጥንቃቄ ተደብቀው" ማግኘቱንም የፖሊሱ መግለጫው ገልጿል።
የተያዙት እሽጎች ባጠቃላይ 40 ሚሊየን ዶላር እንደሚያወጡም ተገምቷል።
በተጨማሪም የጉምሩክ መስሪያ ቤቱ 14.2 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ 95 ጥቅሎችንም መያዙን አስታውቋል።
በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር አቅራቢያ በሚገኘው ብሌዝ ዲአግ የተሰኘው አየር ማረፊያም ቅዳሜ እለት 2.3 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ 18 ኪሎግራም ኮኬይን መገኘቱ ተገልጿል፡፡
አደንዛዥ ዕፆቹ ባለቤት በሌላቸው ሻንጣ ውስጥ ታሽገው ከሴኔጋል አዋሳኝ አገር ወደ አውሮፓ ህብረት አገራት እየተወሰዱ እንደነበርም ተመልክቷል።
መድረክ / ፎረም