በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስን ለረዱ የአፍጋኒስታን ዜጎች ተጨማሪ ቪዛ ተጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ የአፍጋኒስታን ስደተኞች በኢስላማባድ፤ እአአ ሃምሌ 21/2023
ፎቶ ፋይል፦ የአፍጋኒስታን ስደተኞች በኢስላማባድ፤ እአአ ሃምሌ 21/2023

ከዲሞክራቲክና ሪፐሊካን ፓርቲዎች የተወጣጡ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት፣ የአሜሪካ ረጅሙ ጦርነት ነው በተባለው የአፍጋኒስታን ጦርነት ወቅት ከዩናይትድ ስቴትስ ጎን ለቆሙ የአፍጋኒስታን ዜጎች የሚሰጡ ተጨማሪ ቪዛዎች መኖራቸውን የምክር ቤቱ መሪዎች እንዲያረጋግጡ አሳሰቡ።

ከበርካታ የዲሞክራትና የሪፐብሊካን ምክር ቤት አባላት የተጻፈውን ደብዳቤ የተመለከተው አሶሽየትድ ፕሬስ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ዩናይትይት ስቴትስ ለአፍጋኒስታን ዜጎች የምትሰጠውን የልዩ ስደተኞች ቪዛ መጠን ከፍ ማድረግ እንዳለባት ሴናተሮቹ አሳስበዋል፡፡

20ሺሕ ተጨማሪ ቪዛዎች ዓመታዊ በጀቱ ከማለቁ መስከረም ወር በፊት እንደሚያስፈልግም ሴናተሮቹ ተናግረዋል።

በኒው ሃምፕሸር የዲሞክራቲክ ፓርቲውን የሚወክሉት ሴነተር ጄን ሻሂን የሚመሩት የሕግ አውጭዎቹ ቡድን "ይህ ወሳኝ መርሃ ግብር እስካሁን በአፍጋኒስታን የነበረውን ተልዕኮ በመደገፍ ከዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋራ በጀግንነት እና በክብር ያገለገሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አፍጋኒስታን ህይወት ታድጓል" ሲሉ ለህግ መወሰኛው ምክር ቤት መሪ ቻክ ሹመር እና ለሪፐብሊካኑ መሪ ሚች መካነል በጻፉት ደብዳቤ አስታቀውዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ማቲው ሚለርም ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ፣ ምክር ቤቱ የቪዛ መጠኑን እንዲጨምር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው “ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ በመሆን ህይወታቸውን አሳልፈው ለመሰጠት ለተሰለፉ አፍጋኖች ያለብንን ግዴታ እንድንወጣ ያስችለናል፣ ጨርሰው የተረሱ አለመሆናቸውንም ያረጋግጣል” ብለዋል፡፡

ከቪዛው አሰጣጥ መርሃ ግብር ምሥረታ ጀምሮ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ቪዛዎች ብቁ ለሆኑ አፍጋኖች ተሰጥተዋል ሲል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

የቪዛዎቹ አለመሰጠት በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍጋኒስታን ዜጎችን ለአደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

ለአፍጋኒስታን ስደተኞችና የቪዛ ጠያቂዎ የሚሟገተው ድርጅት ዳይሬክተር አንድሩ ሱሊቫን ከተመደበው ቪዛ ውስጥ አሁን የቀረው 7ሺሕ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“አሁን ባለው መጠን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪዛውን የሚሰጥ እንኳ ቢሆን በዚህ የበጋ ወር መጨረሻ ላይ ሁሉም ያልቃል” ያሉት ሱሊቫን “ምክር ቤቱ በቶሎ ውሳኔ ካልሰጠ ወደ ኋላ የሚተውት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አፍጋኖች የራሳቸው ጥፋት ባልሆነ ጉዳይ ለአደጋ ይጋለጣሉ” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG