በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ4 የአፍሪካ ሀገሮች ጉብኝት ሲያደርጉ የቆዩት አሜሪካውያን ሴናተሮች


ፎቶ ፋይል፡- የዴላዌር ሴናተር ክሪስ ኮንስ
ፎቶ ፋይል፡- የዴላዌር ሴናተር ክሪስ ኮንስ

አሜሪካ ለአህጉሪቱ ያላትን ቁርጠኝነት ለማሳየት በአራት የአፍሪካ ሀገሮች የአንድ ሣምንት ጉብኝት ሲያደርጉ የቆዩት የሁለቱም ፓርቲዎች ሴናተሮች ወደ ዋሺንግተን ተመልሰዋል።

አሜሪካ ለአህጉሪቱ ያላትን ቁርጠኝነት ለማሳየት በአራት የአፍሪካ ሀገሮች የአንድ ሣምንት ጉብኝት ሲያደርጉ የቆዩት የሁለቱም ፓርቲዎች ሴናተሮች ወደ ዋሺንግተን ተመልሰዋል።

አራቱ ዴሞክራቶችና አንድ ሪፖብሊካን ሴናተር ያሉበት አሜሪካውያኑ የልዑካን ቡድን በቡርኪና ፋሶ፣ በኒዤር፣ በደቡብ አፍሪካና በዚምባብዌ ጉብኝቱ ወቅት ከፖለቲካ ከሃይማኖት፡ ከንግድና ከወታደራዊ መሪዎች ጋር ተወያይቷል።

ዴሞክራቱ የዴላዌር ሴናተር ክሪስ ኮንስ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ “የጉብኝታችን ዓላማ በአፍሪካና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከር የሚኖረውን ጠቀሜታ ለማጉላት ነው” ብለዋል። በሁሉም ሃገሮች ሞቃት አቀባበል እንደተደረጉላቸውና ጉዟቸው ስኬታማ መሆኑንም አስረድተዋል።

ሴናተር ክሪስ ኮንስ አክለው ግን የልዑካን ቡድኑ ስለ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና አፍሪካን አስመልክተው ስላላቸው አሉታዊ አመለካከት እንዲሁም እስካሁን የአምባሳደሮች ቦታ ያለመሟላት በግንኙነቶች ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አንደምታ ጥያቄዎች ቀርቦለት እንደነበር አልሸሸጉም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG