በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ም/ቤት የውጭ ግንኙነቶች ንኡስ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ


ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ኮሚቴ አመራር አባላት በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ያለው ወታደራዊ ግጭት በሰላም እንዲበቃ ያበረታቱበትን አቋም ያንጽባረቁበትን ረቂቅ ይፋ አደረጉ።

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሲቪሎችን ደህንነት፤ ዲሞክራሲና የሰብዓዊ ጉዳዮች የሚመለከተው የውጭ ግንኙነቶች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የአይዳሆ ክፍለ ግዛቱ የሪብሊካን እንደራሴ ጂም ሪሽ እና የሜሪላንዱ የዲሞክራት ፓርቲ እንደራሴ የኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር ቤን ካርዲን በትላንትናው ዕለት በጋራ ባወጡት በዚህ አቅቋማቸው ሁሉም ዓይነት ግጭቶች እንዲቆሙ፤ ለኢትዮጵያውያን የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እንዲያደርጉ እና ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያፈላልጉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በትግራይ ያለው ግጭት የከፋ ሰብዓዊ ሁኔታ እና በታሪካዊው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ላይ ቀጠኛ አደጋ ይደቅናል” ያሉት ሪች “የሁለቱ ፓርቲዎች በጋራ ያወጡት ይህ አቋም በፕሬዝዳንት አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ሕዝብ ነታ አውጭ ግንባር በልዩነቶቻቸው ዙሪያ እንዲነጋገሩ ለግጭቶቹ ሰላማዊ እና ዘለቂ መቋጫዎችን እንዲያበጁ ያበረታታል ብለዋል። የተረጋጋችና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለሠፊው የአህጉሩ አካባቢዎች ወሳኝ መሆኗን ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ የያዘችውን የዲሞክራሲ ኝባታ ጥረት በመተማመን መንፈስ መርዳቷን ትቀጥላለች።” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው ተናገረዋል.።

“በትግራይ እየተካሄደ ያለው ግጭት በሺዎች የተቆጠሩ ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል። እጅግ የገነነ መጠን ያለው ሰብዓዊ ቀውስ በመፍጠር የኢትዮጵያን መረጋጋት ዘለቄታ ብቻ ሳይሆን የመላውን የአህጉሩን አካባቢም ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው።” ያሉት ደግሞ ካርዲን ናቸው።

“ለኢትዮጵያውያን እና በዩናይትድ ስቴትስ የእንደራሴዎች ምክር ውስት በታላቅ ኩራት የምወክላቸው የሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ነዋሪ የሆኑ ቤተሰቦቻቸው ብዙዎች ሲባል ግጭቱ መቆም አለበት። በግጭቱ ያሉ ሁሉም ወገኖች በመተባበር እርቅ ለመፍጠር - ፍትህ እና ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው።” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG