በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የም/ቤቱ የበጀት ህግ የፌዴራል መንግሥቱን ተቋማት ከመዘጋት አዳናቸው


ካፒቶል
ካፒቶል

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ቋሚ የበጀት ሥምምነት እስኪደረስ ድረስ የፌዴራል መንግሥቱን እስከ ጥር 26 ድረስ የሚያቆየው በጀት በትናንትናው ዕለት 69 በ28 በሆነ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ቋሚው የበጀት ሥምምነት የፕሬዚዳንት ባይደንን አስገዳጅ የክትባት መርሃ ግብር ያካተተ ነው በሚል ተቃዋሟቸውን ባሰሙ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት አማካይነት ሳያስማማ ቀርቷል፡፡

የበጀት ህጉ ረቂቅ ዛሬ ወደ ፕሬዚዳንት ባይደን በማምራት በፊርማቸው ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ ከውሳኔው የደረሰው፣ የተወካዮቹ ምክር ቤት ቀድም ብሎ ከአፍጋኒስታን እንዲወጡ የተደረጉ ሰዎችን መርጃ የሚውል፣ 7ቢሊዮን ዶላርን ጨምሮ ፣አሁን ያለው በጀት ለ11 ተከታታይ ሳምንታት እንዲቀጥል ስምምነት በመገኘቱ መሆኑ ታውቋል፡፡

የበጀት ህጉ እስከዛሬ ዓርብ ድረስ ባይጽድቅ ኖሮ፣ የፌደራል መንግሥት ተቋማት ሊዘጉ እንደሚችሉ ተሰግቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG