የዩናይትድ ስቴትስ የእንደራሴዎች ምክር ቤት ለአንድ ሳምንት ያህል የዘለቀ ክርክር ካካሄደ እና ዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ሃገራት ያላትን ሚና አስመልክቶ በተለይ በሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የፖለቲካ ልዩነት ካስተናገደ በኋላ ነው የ95.3 ቢሊዮን ዶላሩን እርዳታ ያጸደቀው።
ለዩክሬን የታቀደውን የ60 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አጥብቀው የተቃወሙ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ‘ዩናይትድ ስቴትስ ይህን መሰል ከፍተኛ መጠን ያለው እርዳታ ወደ ውጭ አገራት ከመላኳ አስቀድማ በራሷ ችግሮች ላይ ትኩረት ማድረግ አለባት’ የሚለውን የተቃውሞ መከራከሪያ በማሰማት ለሊቱን ሙሉ የምክር ቤቱን መድረክ ተቆጣጥረው አሳልፈዋል።
ይሁንና በምክር ቤቱ ያሉ የዴሞክራት ፓርቲ አባላት በሙሉ እና ለዩክሬይን የሚሰጠውን እርዳታ ማቋረጥ ወይም ዩክሬይንን ቸል ማለት የሩስያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ይበልጥ ሊያጠነክር እና ‘የአገራችንን ብሄራዊ ደህንነትም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል’ የሚል መከራከሪያ ያሰሙ የተወሰኑ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት ድጋፋቸውን በመስጠት የእርዳታ እቅዱን አጽድቀዋል።
መድረክ / ፎረም