ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ተቋም - ሲአይኤ ዋና ዳይሬክተር እንዲሆኑ በፕሬዚዳንት ትረምፕ የታጩት ጂና ሃስፐል ሹመት ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ድምፅ ሊቀርብ ነው።
የሃስፐልን ሹመትና ታሪካቸውን እየመረመረ የቆየው የምክር ቤቱ ቡድን 10 ለ 5 በሆነ ድምፅ የሹመቱን ሃሣብ ዛሬ ተቀብሎ አሳልፏቸዋል።
አሃሁን የሲአይኤ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሆነው እያገለገሉ ያሉትን ጂና ሃስፐልን ሹመት በምክር ቤቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይደግፋሉ ከተባሉት ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ጋር ቢያንስ አምስት ዴሞክራቶች ሳይቀላቀሉ እንደማይቀር ተሰምቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ