ከፍተኛው የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለሥልጣን እንዲሆኑ በትራምፕ የታጩት ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ጁኒየር፣ የእጩዎች ስያሜ በሚጸድቅበት ሥነ ስርዐት ከምክር ቤቱ የፋይናንስ ጉዳዮች ኮሚቴ የውሳኔ ድምጽ ወደሚሰጠው ሙሉ ምክር ቤት አለፉ። በዚህም የሂደቱን የመጀመሪያ መሰናክል ለማለፍ በቅተዋል።
በአካባቢ ጉዳዮች ላይ ካተኮረ የጥብቅና ሞያ ወደ ኅብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ጉዳዮች ተቺነት የተሸጋገሩት ኬነዲ በጤና አገልግሎት ዙሪያ በሚወስዷቸው አወዛጋቢ አቋሞች የሚታወቁ ናቸው።
ክትባቶች ለጤና የሚበጁ መሆናቸውን አስመልክቶ ‘ጥርጣሬዎችን በመዝራት’ የሚወቅሷቸው ተችዎች፣ በመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ላይ ክሶችን በማቅረብ ትርፍ ለማግኘት የሚያስችል ጥረት ያደርጉ ይሆናል’ የሚል ስጋት አላቸው።
ከዲሞክራት ፓርቲው ወገን ሆነው ረዥም ዘመን የዘለቁት ኬነዲ፣ በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ቢሳተፉም፤ በሪፐብሊካን አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረግ የሚያስችል የመንግስት ሥልጣን ለማግኘት በመወሰን ትራምፕን በመደገፍ ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸው ይታወሳል። ኬኔዲ ሹመታቸው ከጸደቀ ክትባቶችን ጨምሮ ሃገር አቀፍ የጤና መርሆዎችን እና የኅብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ዘመቻዎችን የሚቆጣጠሩ ከፍተኛው የጤና ባለ ሥልጣን ይሆናሉ።
መድረክ / ፎረም