በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
አሥራ ሦስት ታጋቾችን ማስለቀቁን የጭልጋ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽሕበት ቤት አስታወቀ 

አሥራ ሦስት ታጋቾችን ማስለቀቁን የጭልጋ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽሕበት ቤት አስታወቀ 


ፎቶ ፋይል፦ ጎንደር፤ ኢትዮጵያ
ፎቶ ፋይል፦ ጎንደር፤ ኢትዮጵያ
አሥራ ሦስት ታጋቾችን ማስለቀቁን የጭልጋ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽሕበት ቤት አስታወቀ 
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

ባለፈው እሁድ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም 18 ሰዎችን አሳፍሮ ከጎንደር አዘዞ ወደ መተማ በመሄድ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በወረዳው “ናረው ዳርጋ” በተባለ ቀበሌ ልዩ ስሙ አውዳዳ ጎጥ ላይ የታጠቁ ኃይሎች ተኩስ በመክፈት 13 ተሳፋሪዎችን አግተው ወደ ጫካ በመውሰድ ላይ እያሉ የአካባቢው የፀጥታ ኅይል በደረሰው ጥቆማ መሰረት እገታው በተፈፀመ በ90 ደቂቃ ውስጥ ታጋቾችን ማስለቀቅ እንደቻለ የጭልጋ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽሕፈር ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መላኩ አብዬ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል። የፀጥታ ሀይሉ ከጋቾቹ ጋራ የተኩስ ልውውጥ ማድረጉንም አመልክተዋል።

መሰል ወንጀሎችን ለመከላከል ህዝቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋራ ተባብሮ እንዲሠራም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል :

በሚኒባሱ ተሳፍሮ የነበረና ኋላም ከእገታ ያመለጠ አንድ ግለሰብ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ከሞት እንደታደገው ገልጿል::

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG