በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማልያው ፍንዳታ የደህንነት አዛዡ ተገደሉ


ሶማልያ ውስጥ ከሞቃድሾ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አፍጎዬ ከተማ ከመንደር ዳር የተቀበረ ፈንጂ የሶማልያ ደህንነት አዛዥና ሲቪሎችን መግደሉ ነገረ፡፡

መሀመድ አህመድ ማዶቤ የተገደሉት ያለቡት ተሽከርካሪ በጥበቃ ኬላ አቅራቢያ ሲደርስ በደረሰበት ፍንዳታ መሆኑን ለደህንነቱ ሲባል ስሙን እንዳይገለጽ የጠየቀ ጋዜጠኛ ወደ ስፍራው በመሄድ ባጠናቀረው ዘገባ አስታውቋል፡፡

በፍንዳታው ሌሎች አራት ሰዎች መቁሰላቸው ተመልክቷል፡፡

አልሻባብ የተባለው አማጺ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን መውሰዱን አስታውቋል፡፡

በሌላም በኩል እዚያው ሞቃድሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ ሌላ ፍንዳታ በጣልያን እስር ቤት ለ17 ዓመታት ታስሮ የተለቀቀ ሀሺ ኦማር ሀሰን የተባለ የሶማሌ ዜጋ መገደሉ ተዘግቧል፡፡

ሀሺ የተገደለው በደቡብ ሞቃድሾ ዳሃርከንሌይ በተባለው አካባቢ መሆኑ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

የሶማሌ ምክር ቤት አባል መሀመድ ኢብራሂም ሞአሊሙ ለቤተሰቡ የማጽናኛ መልዕክት ልከዋል፡፡

በዚህኛው ግድያ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ አለመኖሩ ተነግሯል፡፡

ሟቹ ሀሰን ፣ እኤአ በ1994 ሞቃድሾ ውስጥ በተካሄደው የተኩስ ጥቃት በተገደሉት ኢላሪያ አልፒ እና ሚራን ሆርቫትን በተባሉ ሁለት የጣልያን ጋዜጠኞችን ሞት ተከሶ እኤአ በ2000 ዓም 26 ዓመት ተፈርዶበት እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ እኤአ ጥቅምት 19፣ 2016 በሀሰን ላይ የመሰከረበት ሰው፣ ሶማልያን ለቅቄ ለመውጣት እንድችል ስል የሰጠውት የሀሰት ምስክርነት ነበር በማለቱ ሀሰን ከእስር ተለቋል፡፡

እኤአ 2018 መጋቢት ወር ውስጥ ሀሰን ከቪኦኤ ጋር ባደረገው ቆይታ፣ ያላግባብ በመታሰሩ የ3.1 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ የተከፈለው መሆኑን ቢገልጽም ከደረሰበት ጉዳት ጋር የማይመጣጠን መሆኑን በመገልጽ የጣልያንን መንግሥት ለመክሰስ ማሰቡን ገልጾ ነበር፡፡

አልፒ እና ሆርቫትን የተባሉ ሁለቱ ጋዜጠኞች በተገደሉበት ወቅት፣ የተመረዙ ፍሳሾችን ስለማስወገድና የጦር መሳሪያ ሽያጭን አስመልክቶ የምርመራ ጋዜጠኝነት ሲሰሩ እንደነበር የጣልያን ዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል፡፡

ገዳዮችንና የግድያውን ምክንያት በትክክል ማወቅ አይቻልም በሚል በጣልያን ዐቃቢ ህግ የግድያው ምርመራ ፋይል የተዘጋው እኤአ በ2017 መሆኑ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG