በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ብሊንከን የሱዳንን ጠቅላይ ሚኒስትር አነጋገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክን ዛሬ በቴሌፎን አነጋግረዋቸዋል።

በሱዳን የሰላም ምስረታው ሂደት እንዲሁም የፖለቲካ የጸጥታ እና የኢኮኖሚ ለውጥ ርምጃዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መነጋገራቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ያወጡት መግለጫ አመልክቱዋል።

በተጨማሪም ስለቀጣናዊ መረጋጋት፥ ሱዳን ስለደረሰቻቸው የተለያዩ የሰላም ስምምነቶች እና ከእስራኤል ጋር መደበኛ ግንኙነት ለመጀመር የገባችውን ቃል በተመለከተም ተወያይተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክንና በሲቪሎች የሚመራውን የሽግግር መንግሥት እንደምትደግፍ በድጋሚ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን በድጋሚ ያረጋገጡላቸው መሆኑን የቃል አቀባዩ መግለጫ አውስቷል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የሱዳንን ብሄራዊ አንድነት ለማጠናከር፥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመመስረት እንዲሁም የጦር ኃይሉን ተቋም በማሻሻል ሌሎችንም ኃይሎች ሠራዊቱ ውስጥ ለማዋሃድ እና በተጨማሪም ፍትህ እና ተጠያቂነትን ተግባራዊ ለማድረግ ስለያዙት ውጥን መወያየታቸውን መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG