በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተነጋገሩ


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን/ፎቶ ቪኦኤ/
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን/ፎቶ ቪኦኤ/

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጹሑፍ፤ እርሳቸውና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጦርነቱን የማቆም ሥምምነቱን በአስቸኳይ ተግባራዊ የማድረግ አስፈላጊነትና በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ፣ በአፋርና በአማራ ክልሎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለማድረስና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበረበት ለመመለስ እየሠራ ላለው ሥራ እውቅና እንደሚሰጡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል ቤቱ ዌብ ሳይት የሰፈረው አጭር መግለጫ ያሳያል።

የውጭ ኃይሎች መውጣትና የትግራይ ኃይሎች ትጥቅ መፍታትን ጨምሮ የሠላም ሥምምነቱን በፍጥነት ተግባራዊ የመደረጉን አስፈላጊነት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዳነሱላቸው ተገልጿል።

ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ኅብረት በኩል የተጀመረውን ሂደት ሙሉ ለሙሉ እንደምትደግፍ በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።

XS
SM
MD
LG