በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቶኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተነጋገሩ


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ /ፎቶ፤ ቪኦኤ ፋይል/
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ /ፎቶ፤ ቪኦኤ ፋይል/

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ስልክ ደውለው አነጋግረዋቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስንና የኢትዮጵያን ግንኙነቶች አስፈላጊነት ብሊንከን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአፅንዖት ያነሱላቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ቢሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ባወጣው ፅሁፍ አስታውቋል።

ትግራይ ውስጥ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ በእጅጉ የሚያሳስባቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለፃቸውንና ሌላ የህይወት መጥፋትን ለማስቀረት እንዲቻል መንግሥቱ ፈጥኖ መሉና ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ እንዲያደርግ ማሳሰባቸውን ቃል አቀባዩ አመልክቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የለውጥ አጀንዳ፣ ለመጭው ብሄራዊ ምርጫ፣ ለአካባቢያዊ ሰላም፣ ፀጥታና ደኅንነት፣ ለዴሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለፍትኅና ለተጠያቂነት መስፈን፣ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና ድጋፏን መስጠቷን እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶኒ ብሊንከን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ ያረጋገጡላቸው መሆኑንም የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ፅሁፍ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG