በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ካልዓይ ጌቶች" ዳግ ኤምሆፍ


ካማላ ሃሪስ እና ዳግ ኤምሆፍ
ካማላ ሃሪስ እና ዳግ ኤምሆፍ

ካማላ ሃሪስ የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያዋ ሴት ም/ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመጀመሪያ ወንድ እርሱ ባለሥልጣን ያልሆነ አብሯቸው ዋይት ሃውስ መግባቱ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ቤተሰብ እንደልማድ ሆኖ የመጀመሪያ ቤተሰብ /First Family/ እየተባለ ይጠራል። የፕሬዚዳንቱም ባለቤት የመጀመሪያ ወይም ቀዳሚት ሴት ወይም እመቤትም ይሆናል - First lady ተብላ ትጠራለች። ልጆቻቸውም የመጀመሪያ ልጆች ወይም ቀዳሚ ልጆች ይባላሉ First Children, First Daughter, First Son ይባላሉ፤ በፕሬዚዳንቱ ቤት ውስጥ ያለ ሁሉ የመጀመሪያ ወይም ቀዳሚ ወይም First Man የሚል ተቀጥላ ይሰጠዋል። የመሪው ቤተሰብ ነውና! ፕሬዚዳንቱ እራሱም ቢሆን “የመጀመሪያ ወንድ” ወይም “የመጀመሪያ” ወይም “ቀዳሚ ጌታ” ወይም First Man ሊባል ይችላል።

ውሻውም ወይም ውሻዎችም ቢኖሩ የመጀመሪያ፣ ቀዳሚ፣ First ውሻ ድመቷም እንዲሁ - የመሪው ቤት ሁሉ ቀዳሚ - First ነው በዩናይትድ ስቴትስ ዘልማድ።

በህግ ወይም በወግ የሠፈረ ትዕዛዝ የለም። ስለቀዳሚት እመቤት ካነሳን ዘውዳዊ ሥር ዓት ቢሆን “እቴጌ” እንዲሉ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

"ካልዓይ ጌቶች" ዳግ ኤምሆፍ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:50 0:00XS
SM
MD
LG