በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ የኢቦላ ታማሚ መሆኑ የተረጋገጠ ሰው ህይወቱ አለፈ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ጎማ ከተማ ውስጥ ሁለተኛው የኢቦላ ታማሚ መሆኑ የተረጋገጠው ሰው ህይወቱ ማለፉን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

ዛሬ የህመምተኛው ህይወት ማለፉ ይፋ የደረገው በበሽታው መያዙ በተነገረ ማግሥት ነው።

ሟቹ በቫይረሱ መጠቃቱ የታወቀለት ከኢቱሪ ክፍለ ሃገር የገጠር አካባባቢ ወደጎማ ከተማ ከተጓዘ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደነበር እና ጎማ በሚገኘው የኢቦላ ህክምና ማዕከል ሲታከም እንደቆየ ባለሥልጣናቱ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ቁጥሩ ወደአንድ ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ የሚኖርባት ጎማ፣ ከሩዋናዳ ጋር የምትዋሰን ሲሆን በየቀኑ በአስር ሺዎች የተቆጠሩ ነዋሪዎች በእግር ድንበር እያቋረጡ ይመላለሱባታል።

በቅርቡ አንድ ቄስ ጎማ ከተማ በአውቶቡስ እንደገቡ በኢቦላ ቫይረስ እንደታመሙና ህይወታቸው እንዳለፈ በሽታው ህዝብ በሚበዛባት ከተማ ፈጥኖ ይዛመታል የሚል ሥጋት መቀስቀሱ ይታወሳል።

ያን ድንገት ተከትሎ የዓለም የጤና ድርጅት በብጥብጥ የታመሱት የኮንጎ ሰሜናዊ ኪቩ ኢቱሪ ክፍለ ግዛቶችን የኢቦላ ወረርሺኝ በዓለምቀፍ ደረጃ አሳሳቢ የሆነ አጣዳፊ ህዝብ ጤና ጉዳይ ሲል አውጆታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG