ዋሺንግተን ዲሲ —
ታይላንድ ላይ በአንድ ትልቅ ዋሻ ውስጥ በደረሰው የውሃ መጥለቅልቅ ምክንያት መውጫ አጥተዋል የተባሉትን አሥራ ሁለት በአሥሮች ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የእግር ኳስ ተጫዋቾችንና አሰልጣኛቸዋን የመፈለጉ ጥረት ለአራተኛ ቀን ቀጥሏል።
ልጆቹና አሰልጣኛቸው ከልምምድ ቦታ ሳይመልለሱ ከቀሩ በኋላ ነበር ባለፈው ቅዳሜ መጥፋታቸው የተገለፀው። ዋሻው ውስጥ ፍለጋ የተጀመረው ቢስኪሌቶቻቸውና የኳስ ጨዋታ ጫማዎቻቸው በዋሻው በር አከባቢ ከተገኙ በኋላ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ