በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታንዛኒያ ቪክቶሪያ ሃይቅ ጀልባ ተገልብጦ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ


ትናንት ሃሙስ ከሰዓት በኋላ ቪክቶሪያ ሃይቅ ላይ በተገለበጠው የመንገደኛ ማመላለሻ ጀልባ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል ከአንድ መቶ የሚበልጡ መሞታቸውን የታንዛኒያ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ትናንት ሃሙስ ከሰዓት በኋላ ቪክቶሪያ ሃይቅ ላይ በተገለበጠው የመንገደኛ ማመላለሻ ጀልባ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል ከአንድ መቶ የሚበልጡ መሞታቸውን የታንዛኒያ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የአደጋውን ሰለባዎች ፍለጋ ስራው ዛሬም ቀጥሏል። እስካሁን ቢያንስ ሰላሳ ሰባት ሰዎች በህይወት ለማትረፍ መቻሉን የገለጹት የታንዛኒያው የአካባቢው ኮሚሽነር ጆን ሞንጌላ አንዳንዶች እጅግ በከፋ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ያመለከቱት ።

በጀልባዋ ላይ የነበሩትን ተሳፋሪዎች ቁጥር በግምት ለመናገር ባልፈልግም በሃይቁ ላይ የሚጓጓዙት ጀልባዎች በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎችን ማሳፈራቸው የተለመደ ነው ብለዋል። የታንዛኒያ የሀገር ውስጥ የዜና ማሰራጫዎች እንዳሉት ከሆነ በተገለበጠው ጀልባ ላይ ሁለት መቶ ተሳፋሪዎች ነበሩ።

በመንግሥቱ ራድዬ ዜና መሰረት ተሳፋሪዎቹ የተነሱት ኡኬሬዌ ደሴት ላይ ከሚገኘው ቡጎሎራ ከተማ ሲሆን ወደሌላዋ ደሴት ሲጓዝ ነው የተገለበጠው። የአደጋው መነሾ ባይገለጽም ካሁን ቀደም ለደረሱ ተመሳሳይ አደጋዎች ምክንያቱ ብዙውን ጊዜ ከልክ በላይ ተሳፋሪ መጫን መሆኑ ይታውቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG