በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳይንቲስቶች ጥያቄ በኮቪድ-19


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስ ከአየር በትንፋሽ ከሰው ወደሰው መተላለፉን የሚመለከተውን የካሁን ቀደሙን ምክረ ሃሳቡን እንዲያሻሽል ሳይንቲስቶች ጠየቁ።

ጥያቄውን ያቀረቡት ከ32 ሃገሮች የተሰባሰቡ 239 ሳይንቲስቶችን ያቀፈ ቡድን መሆኑ ተገልጿል።

ሳይንቲስቶቹ ቫይረሱ ከያዛቸው ሰዎች በሳልና በማስነጠስ የሚወጣ ቫይረስ አየር ላይ እይተዘዋወረ ሊቆይ እንደሚችል፤ መጠኑ ትንሽ/ኢምንትም/ ቢሆንም ወደሌላ ሰው ሊዛመት እንደሚችል ማሰርጃ እንዳለ ይገልጻሉ።

የዓለም የጤና ድርጅት እስካሁን ባለው ምክረ ሃሳብ መሰረት ቫይረሱ በትንፋሽ ወደሰው ሊገባ የሚችለው ከታመመ ሰው በሳልና በማስነጠስ ወደአየር በሚረጭ በዛ ያለ ፈሳሽ እንደሆነና መጠኑ ትልቅ ሲሆን ደግሞ ፈጥኖ አየር ላይ ሳይቆይ ይወድቃል።

ይህ በእንዲህ እያለ ሳውዲ አረብያ በየዓመቱ 2.5ሚሊዮን የእስልምና እምነት ተከታዮች ለሚያሰባስበው የሃጂ ጉዞ ዘንድሮ ለ1ሺህ ምዕመናን ብቻ እንደሚፈቀድ ወስናለች፤ ዘንድሮ ለውጪ ሃገር ተጓዥች ዝግ መደረጉም ታውቋል።

XS
SM
MD
LG