በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ይድረስ ለሰማይ አፍቃሪያን


ሰኔ 7 እና ሰኔ 8 / 2009 ዓ.ም. (ትናንትናና ዛሬ መሆኑ ነው) እንዲያውም ሰሞኑንም ሁሉ ይቀጥላል፤ የሌሊቶቹ ሰማዮች ላይ ፕላኔት ሳተርን ከፀሐይ መውጫና መጥለቂያ አንፃር ጥርት ብላ ትታያለች፡፡

ሰኔ 7 እና ሰኔ 8 / 2009 ዓ.ም. (ትናንትናና ዛሬ መሆኑ ነው) እንዲያውም ሰሞኑንም ሁሉ ይቀጥላል፤ የሌሊቶቹ ሰማዮች ላይ ፕላኔት ሳተርን ከፀሐይ መውጫና መጥለቂያ አንፃር ጥርት ብላ ትታያለች፡፡

ፀሐይ አመሻሹን በምዕራብ ስትጠልቅ ሳተርን በምሥራቅ ብቅ ትላለች፤ ደግሞም በምሥራቅ ብቅ ስትል ሳተርን በምዕራብ ማለዳው ላይ ትጠልቃለች፡፡ ስለዚህም እነዚህ ቀናት የፀሐይና የሳተርን ተቃርኖ ቀናት ተብለው ይጠራሉ፡፡

የሰኔ ሰማዮች ለሥነ-ፈለክ አፍቃሪዎችና ተከታታዮች እጅግ የተዋቡና ባለብዙ ሥራ እንደሆነ ነው የሚሰማው፡፡

በመሸበትና ሰማዩ የጠራ በሆነበት አካባቢ ያላችሁ ወጣ ብላችሁ ሰማዩን ቃኙት፤ እዚያ ወደ ምሥራቁ ሲያዘነብል ጥርት ብላ የምታይዋት ብሩህ ኮከብ - ኮከብ አይደለችም፤ ፕላኔት ሳተርን እንጂ፡፡ ግሩም ቴሌስኮፕ ያለው ደግሞ ቀለበቶቿንም ለመጎብኘት ዕድሉ ይኖረው ይሆናል፡፡

ለማንኛውም ስለመሬታችን የተፈጥሮ አካባቢም ስለሰማዩም የወቅቱን መረጃ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ይድረስ ለሰማይ አፍቃሪያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:23 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG