በአፍሪካ ቀንድ ከአሥር ሚሊየን በላይ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ 4 ነጥብ 5 ሰው ለረሃብ ያጋለጠ ባለፉት ስድሣ ዓመታት ያልታየ የከበደ ድርቅ መከሠቱ ይታወቃል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተቃራኒው ምዕራብ ኢትዮጵያን የከበዱ የጎርፍ ሁኔታዎች እንደሚያሰጉት ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲን የጠቀሱ የሚድያ ዘገባዎች እንደሚሉት በሃገሪቱ ያለውን የድርቅና የረሃብ አጣዳፊ ሁኔታ ያባብሰዋል የተባለው ጎርፍ የሚያሠጋው የኢትዮጵያን ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ አካባቢዎች ነው፡፡
የጣና ሐይቅ፣ የአዋሽ ወንዝና የጋምቤላ አካባቢዎች ይበልጥ ተጋላጭ እንደሚሆኑም መጠቆሙ ተዘግቧል፡፡
ረቡዕ፣ ሐምሌ 13፣ 2003 ዓ.ም. የተደረገውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ስብሰባ እና በኢትዮጵያ ጂዖ-ፊዚክስ፣ ስፔስ ሣይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ላይ የተደረገ ቃለመጠይቅ የያዘውን የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዝግጅት ያዳምጡ፡፡