ዋሺንግተን ዲሲ —
ካሜሩን ውስጥ የሚገኝ የአንድ ፕሪስቢቴሪያን ባለሥልጣን እንዳስታወቁት፣ ዳይሬክተሩን ጨምሮ ከትምህርት ቤት ተጠልፈው የነበሩ 79 ተማሪዎች ተለቀቁ።
ጠለፋው ባሜንዳ ከተባለችዋ ከተማ የተፈጸመው ባለፈው ሰኞ ሲሆን፣ የሰሜን ምዕራብ አካባቢ፣ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ከሆነው መንግሥት ነፃ ለመውጣት የሚታገሉ እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች የሆኑ ነውጠኞች የሚንቀሳቀሱበት መሆኑ ይታወቃል።
ሮይተርስ የዜና አውታር ከአንድ የፕሪስቢቴሪያን ካህን ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ሲዘግብ፣ የተጠለፉት ተማሪዎች ቁጥር 79 ሳይሆን 78 ነው ብሏል። ይህም የሆነው፣ በሮይተርስ ዘገባ መሠረት፣ ጠላፊው ሰው ተማሪ የነበረና እዚያው ከጠላፊዎቹ ጋር የቀረ መሆኑ ተመልክቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ