በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ ት/ቤቶች ሊከፈቱ ነው


የፈረንሳይ ትምህርት ቤቶች ነገ ማክሰኞ ሊከፈቱ ዕቅድ ተይዟል። ይሁን እንጂ ሰሞኑን የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱ እቅዱ ላይ ችግር ደቅኖበታል። በሀገሪቱ በየቀኑ ብዙ ሽህ አዲስ የቫይረሱ ተያዦች እየተመዘገቡ ነው።

ሃኪሞች ስድስት ዓመትና በላይ የሆኑ ተማሪዎች የአፍና አፍንጫ ጭንብል እንዲጠቀሙ ማድረግ እና የተወሰኑትን ትምህርቶች በርቀት በኢንተርኔት አማካይነት ማስተማርን የመሳሰሉ ጥብቅ እርምጃዎች እንዲወሰዱ አሳስበዋል።

የፈረንሳይ የትምህርት ሚኒስትር የተወሰኑት የትምህርት ክፍሎች ነገም እንደተዘጉ እንደሚቆዩ አመልክተዋል።

እስካሁን ባለው ዕቅድ መሰረት ከ11 ዓመት በላይ የሆኑ ተማሪዎች ሙሉ ቀን ጭንብል እንዲጠቀሙ ታዟል፤ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችና ስብሰባዎም ይከለከላሉ።

ቀደም ብሎ በወረርሽኙ ክፉኛ ከተመቱት ሃገሮች እንዷ የሆነችው ጣሊያን በቅርብ ሳምንታት በኮቪድ-19 ምክንያት ጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እንደጨመረ ገልጻለች።

ከአንድ ወር በፊት 38 እንደነበሩ ትናንት ግን የጽኑ ህሙማኑ ቁጥር 86 መድረሱ ነው ያመለከተችው።

XS
SM
MD
LG