በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒጀር ውስጥ ሃያ ተማሪዎች በእሳት አደጋ ሞቱ


በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የደረሰው የንብረት ጉዳት
በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የደረሰው የንብረት ጉዳት

ትናንት ደቡባዊ ኒጀር በሚገኝ ትምህርት ቤት የሳር ጣሪያ ባላቸው መማሪያ ክፍሎች በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ተማሪዎቹ ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስታውቋል።

ሌሎች እስራ አራት ተማሪዎች በቃጠሎው መጎዳታቸውን መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል። የአደጋው መንስዔ ለማወቅ ምርመራ መከፈቱን ነው የገለጸው።

በምዕራብ አፍሪካዋ ሃገር በዚህ የአውሮፓውያን 2021 በትምህርት ቤት ቃጠሎ ሲደርስ ይህ ሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባለፈው ሚያዝያ ወር ዋና ከተማዋ ኒያሜ በሚግኝ ትምህርት ቤት በተነሳ ቃጠሎ ሃያ የመዋዕለ ህጻናት ተማሪዎች መሞታቸው ተገልጿል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ በመግለጫው ከነዚህ ሁለት ቃጠሎዎች በኃላ የመዋዕለ ህጻናት ተማሪዎች በሳር ጣሪያ በተሰሩ መማሪያ ክፍሎች ውስጥ እንዳይማሩ መከልከሉን አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG