በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በምገባ ፕሮግራም 5.3 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመገብ ተችሏል” - ትምህርት ሚኒስቴር


“በምገባ ፕሮግራም 5.3 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመገብ ተችሏል” - ትምህርት ሚኒስቴር
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:23 0:00

በኢትዮጵያ በመተግበር ላይ በሚገኘው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ከትግራይ ውጪ ባሉ ክልሎች ከ 5.3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመገብ እንደተቻለ የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ፡፡

በአፍሪካ ኅብረት ጽሕፈት ቤት በተከበረው ስምንተኛው የአፍሪካ ት/ቤት ምገባ ቀን ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ መንግሥት የት/ቤት ምገባ ፕሮግራምን በልማት ፖሊሲው ማካተቱን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው አስተዳደራቸው በዓመት 4.6 ቢሊዮን ብር በመመደብ 700 ሺህ ተማሪዎችን እየመገበ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ኅብረት የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሐመድ ቤልሆሲን፣ በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2022 ዓመተ ምህረት በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም በአፍሪካ 66 ሚሊዮን ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ያመለከቱ ቢሆንም፣ ይህ አሃዝ በምገባ ፕሮግራሙ መካተት ከነበረባቸው ተማሪዎች ውስጥ 31 ከመቶ ብቻ እንደሚይዝ ጠቅሰዋል፡፡ በአዲስ አበባው የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች፣ ምገባው ትኩረታቸውን ትምህርት ላይ እንዲያደርጉ እንዳገዛቸው እና የቤተሰብ ወጪን እንደቀነሰላቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG