በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምግብ ቀውሱ አስጊ መሆኑን ሴቭ ዘ ችልድረን አሳሰበ


የምግብ እርዳታ ጠባቂዎች - በኢትዮጵያ /ፎቶ - ፋይል/
የምግብ እርዳታ ጠባቂዎች - በኢትዮጵያ /ፎቶ - ፋይል/

ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የምግብ ቀውስ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ዓለምአቀፉ ግብረሰናይ ድርጅት ሴቭ ዘ ችልድረን አስጠንቅቋል፡፡

የምግብ ቀውሱ መበርታቱን ሴቭ ዘ ችልድረን አሳሰበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ለሃምሣ ዓመታት ያህል ጊዜ ታይቶ የማያውቅ ብርታት የነበረው ድርቅ ኢትዮጰያ ላይ ያስከተለው ጉዳት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ ስለሚባባስ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምላሽ ወሳኝ መሆኑን ሕፃናት አድን ድርጅት አሳስቧል፡፡

ድርጅቱ ዓርብ፤ ሐምሌ 1 /2008 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አምስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሃምሣ ሺህ ህፃናትን ጨምሮ ከአሥር ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን በህዳር የሚጠበቀው የመኸር ምርት እስኪደርስ የሚተማመኑት በዕለት ደራሽ እርዳታ ላይ ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለአደጋ እጅግ የተጋለጡትን ለመርዳት የተደረገው ጥረት የተሳካ እንደነበር ያመለከተው ይኸው መግለጫ የህፃናት አድን ድርጅት በድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጆን ግራሃም የተጀመረው ጥረት መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸውን ጠቅሷል።

የክረምቱ ዝናብ አለመቅረቱ መልካም ዜና ቢሆንም ሰብሎቻቸው በተደጋጋሚ የመከኑባቸው ቤተሰቦች በአካልም በገንዘብም ክፉኛ መዳከማቸውን የድርጅቱ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

የህጻናት መርጃ ድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር “በሚቀጥሉት ሦስት ወራት የምናደርገው ሁሉ አስከፊ ረሃብ እንዳይከሰት ለመከላከል ባለፉት ወራት ያደረግነው ርብርብ የመጨረሻውን መልካም ፍሬ የሚያፈራበት ወይም ተቃራኒው የሚከሰትበት ይሆናል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ

XS
SM
MD
LG