በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ አጣዳፊ የምግብ ዋስትና ተደቅኗል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በደቡባዊ እና በምስራቃዊ አፍሪካ በብዙ ሚሊዮኖች የተቆጠረ ህዝብ አጣዳፊ የምግብ ዋስትና ችግር እንደተደቀነበት ተጠቆመ፡፡

በደቡባዊ እና በምስራቃዊ አፍሪካ በብዙ ሚሊዮኖች የተቆጠረ ህዝብ አጣዳፊ የምግብ ዋስትና ችግር የተደቀነበት መሆኑን እና የዚህም ተግዳሮት ከፊል ምክንያቱ የአየር ንብረት ለውጥ መሆኑን ህጻናት አድን የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት አስገነዘበ፡፡ ለችግሩ ከተጋለጡት ግማሹን አሃዝ የሚይዙት ልጆች መሆናቸውን አክሎ ገልጿል።

አካባቢዎቹ በቅርብ ዓመታት በከባድ አውሎ ንፋሶች ጎርፎች እና በድርቅ በተደጋጋሚ የተመቱ ሲሆን በነዚያ አካባቢዎች የአየር ግለቱ ከሌሎች የዓለም አካባቢዎች በፈጠነ መልኩ እየጨመረ መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ።

እአአ በ2019 በሁለቱ የአፍሪካ አካባቢዎች የአየር ንብረት ቀውስ ከባድ ውድመት ያደረሰበት ተብሎ የሚታወስ እንደሚሆን የተናገሩት የህጻናት አድን ድርጅት የዓለምቀፍ ሰብዓዊ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጋብሪየላ ዋጅማን በአህጉሪቱ ቢያንስ ሰላሳ ሶስት ሚሊዮን ህዝብ ለአጣዳፊ የምግብ ችግር ተጋልጧል ብለዋል።

እአአ በ2015 የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ በበይነ መንግሥታዊ ኮሚቴ የተደረገ ጥናት ደቡባዊ አፍሪካ ውስጥ የአየር ግለቱ መጠን በተቀረው የዓለም ክፍል ካለው እጥፍ እንደሆነ አስገንዝቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG