በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲ ተወላጅ ስደተኛ በታይላንድ


ራፋሕ ሞሐመድ አል ኩኑንን
ራፋሕ ሞሐመድ አል ኩኑንን

የተባበትሩት መንግሥታት ድርጅት የሰደተኞች ጉዳይ አገልግሎት ወደ ታይላንድ ያመለጠችውን የ18 ዓመት ዕድሜ የሳዑዲ ተወላጅ ስደተኛ መሆንዋን ካረጋገጠ በኋላ አውስትራልያ ጥገኝነት እንድተሰጣት ጠይቋል።

የተባበትሩት መንግሥታት ድርጅት የሰደተኞች ጉዳይ አገልግሎት ወደ ታይላንድ ያመለጠችውን የ18 ዓመት ዕድሜ የሳዑዲ ተወላጅ ስደተኛ መሆንዋን ካረጋገጠ በኋላ አውስትራልያ ጥገኝነት እንድተሰጣት ጠይቋል።

የአውስትራልያ የሀገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስቴር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽነር በጠየቀው መሰረት ራፋሕ ሞሐመድ አል ኩኑንን ጥገኝነት ለመስጠት እንደሚያስብበት ገልጿል።

ወጣትዋ ከቤትሰብዋ ጋር ወደ ኩዌት ለዕርፈት ከሄደች በኋላ አምልጣ ቅዳሜ ማታ የታይላንድ አውሮፕላን ማረፍያ ላይ ገባች።

ወጣትዋ በአይሮፕላን ማረፍያው ሆቴል ውስጥ መሽጋ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰዎች ጋር እስከምነጋገርበት ጊዜ ድረስ አልወጣም በማለት በርካታ የትዊተር መልዕክቶች አስተላልፋለች። የታይላንድ ኢሚግረሽን፣ ወደ ሀገርዋ ለመመለስ የነበረውን ዕቅድ ቀለበሰ።

ቤተሰቦቼ በጣም ጥብቅ ከመሆናቸው የተነሳ ጸጉሬን በመቁረጤ ብቻ ለስድስት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ዘግተዋብኛል። አሁን ብመለስ ከሳዑዲ ዓረብያ እሥር ቤት እንደወጠሁ ይገድሉኛል ብላ ነበር።

የወጣትው አባትና ወንድምዋ ትላንት ባንኮክ ገብተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG