በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዜጠኛው ግድያ የተጠረጠሩ የሞት ቅጣር እንዲፈረድባቸው ተጠየቀ


በቅርቡ ቱርክ ኢስታንቡል ከተማ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ቆንስላ ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ የገደሉ ተብለው የተጠረጠሩት አምስት ሰዎች የሞት ቅጣት እንዲፈረድባቸው የሳዑዲ ዓረብያ አቃቤ ህግ ጠየቁ።

በቅርቡ ቱርክ ኢስታንቡል ከተማ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ቆንስላ ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ የገደሉ ተብለው የተጠረጠሩት አምስት ሰዎች የሞት ቅጣት እንዲፈረድባቸው የሳዑዲ ዓረብያ አቃቤ ህግ ጠየቁ።

የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አምደኛና የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ነቃፊ የነበረው ኻሾግዢ ባለፈው እኤአ ጥቅምት ሁለት ሳዕዲው ቆንስላ ውስጥ መገደሉ ይታወሳል።

ዛሬ የአቃቤ ህጉ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ ኻሾግዢን የሚገድል መርዝ በመርፌ ወግተውት ሲሞት አስከሬኑን ቆራርጠውታል ብለዋል።

ኻሾግዢ ቆንስላው ከገባ በኋላ ደብዛው የጠፋው ጋዜጠኛው ምን እንደሆነ የሳዑዲ መንግሥት የተለያየ መግለጫ ሲሰጥ ቆይቷል። ከቆንስላው ራሱ ወጦ ሄዷል፣ ድብድብ ተከስቶ በዚያ መሃል ህይወቱ አልፏል፣ ጋጠ ወጦች በራሳቸው ተነሳስተው ገድለውታል ሲል ቆይቷል።

አቃቤ ህግ የሞት ቅጣት እንዲበየንባቸው የጠየቀው ኻሾግዢ እንዲገደል ትዕዛዝ በሰጡና ወንጀሉን በፈጸሙ ተከሳሾች ላይ መሆኑን ገልጾ ሊሎች ከወንጀሉ በተያያዘ የተከሰሱ ስድስት ሰዎች ደግሞ እንደየአግባቡ ቅጣት እንዲበየንባቸው ጠይቀናል ብሏል።

ሳዑዲ ትሩክን በግድያው ጉዳይ ያሏትን ማስረጃዎችና ሌሎችም መረጃዎች በመስጠት እንድትረዳት መጠቋሟ ተገልጿል። ቱርክ ቀስ እያለች ስለጉዳዩ ያላትን መግለጫ ይፋ እያደረገች መሆኑዋ ይስተዋላል። የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን “ኻሾግዢን ግደሉ” የሚለው ትዕዛዝ የተሰጠው በእጅግ ከፍተኛ የሳዑዲ መንግሥት ባለሥልጣናት ደረጃ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

የሳዑዲ ባለስልጣናት የአልጋ ወራሽ ሳልማን እጅ የለበትም በማለት አስተባብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG