በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በተካሄደው የአየር ጥቃት ሠላሳ ሰዎች ተገደሉ


የመን ዋና ከተማ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ዛሬ በተካሄደው የአየር ጥቃት ቢያንስ ሠላሳ ሰዎች ተገደሉ።

የመን ዋና ከተማ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ዛሬ በተካሄደው የአየር ጥቃት ቢያንስ ሠላሳ ሰዎች ተገደሉ።

ሰንአ ውስጥ ባለው የፖሊስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ በሽምቅ ተዋጊዎች ቁጥጥር ሥር ባለው ፖሊስ ጣቢያ ላይ ዛሬ ረቡዕ ማለዳ በተካሄደው በዚሁ የአየር ጥቃት፣ ከሞቱት ሌላ ቢያንስ 80 ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል።

ጥቃቱ የተካሄደው በሳውዲ መራሹ ጣምራ ኃይል ሲሆን፣ ዒላማ ያደረገውም የሽምቅ ተዋጊዎቹን ይዞታ እንደሆነ ተመልክቷል።

ይህ እአአ በ2015 የተጀመረውና የተመድ ኃላፊው አንቶንዮ ጉተሬዥ ባለፈው እሑድ፣ “ትርጉም የለሽ” ያሉት ጦርነት እንዲያበቃ ማሳሰባቸው አይዘነጋም።

የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲሌርሴን ባለፈው ዐርብ ሲናገሩ፣ ሳውዲ አረቢያ የመን ውስጥ የምታደርገውን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንድታቆም ማሳሰባቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG