በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲ ንጉሥ ሳልማን ሹም ሽር አድረጉ

የሳዑዲ አረቢያዊው ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ ኢስታንቡል ቱርክ ውስጥ መገደል ዓለምቀፍ ቁጣና ንዴትን ከቀሰቀሰ ከሦስት ወራት በኋላ የሳዑዲው ንጉሥ ሳልማን ሹም ሽር አድርገው መንግሥታቸውን በአዲስ መልክ ማዋቀራቸውን አስታወቁ።

የሳዑዲ አረቢያዊው ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ ኢስታንቡል ቱርክ ውስጥ መገደል ዓለምቀፍ ቁጣና ንዴትን ከቀሰቀሰ ከሦስት ወራት በኋላ የሳዑዲው ንጉሥ ሳልማን ሹም ሽር አድርገው መንግሥታቸውን በአዲስ መልክ ማዋቀራቸውን አስታወቁ።

ንጉሡ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሥልጣን ላይ የነበሩትን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብደል አጅ-ዡቤይርን አንስተው በመንግሥት ጉዳዮች ሚኒስትሩ ኢብራሂም አል-አሳፍ ተክተዋቸዋል።

አጅ ዡቤይር ከሥልጣናቸው ዝቅ ተደርገው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል።

የብሄራዊ ዘብ አዛዡን ልዑል ሚቴብ ቢን አብዱላህንም በልዑል አብዱላ ቢን ባንዳር ቢን አብዱልአዚዝ ተክተዋል።

ንጉሥ ሳልማን በተጨማሪም የሃገሪቱ የፖለቲካና ደኅንነት ምክር ቤት በአዲስ ሁኔታ እንዲዋቀር አዝዘዋል።

ካሊድ ቢን ቂራርን የደኅንነቱ ጠቅላይ አዛዥ፣ ሙሳየድ አል አይባንን የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪያቸው አድርገው ንጉሡ ሾመዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG