በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከጋዜጠኛ ጃማል ግድያ ጋር በተያያዘ የሞትና የእስር ውሳኔ ተሰጠ


ኢስታንቡል በሚገኘው የሳውዲ ኤምባሲ በጋዜጠኛ የጃማል ኻሾጊ ላይ ከተፈጸመው ግድያ ጋር በተያያዘ ሳዑዲ አረቢያ ያስቻለው ፍርድ ቤት አምስት ሰዎች በሞት ሦስት ሌሎች ደግሞ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጠ።

የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው ግድያውን የፈጸሙና በድርጊቱ በቀጥታ የተሳተፉ መሆናቸውን የገለጹት አቃቤ ህጉ የእስር ቅጣት የተሰጣቸው ደግሞ ወንጀሉን ለመሸፋፈን በተጫወቱት ሚና ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

የፍርድ ሂደቱ በአመዛኙ በሚስጥር ሲካሄድ ከቆየ በኋላ ነው ዛሬ የቅጣት ውሳኔው የተሰጠው። የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን የቀድሞ ዋና ረዳት ሳኡድ አል ካታኒ በካሾጊ ግድያ ወንጀል ነፃ ተብለዋል።

ቢሮው ፓሪስ የሆነው የጋዜጠኞች ደኅንነት ተከታታዩ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች (ራፖርቲዬ ሳን ፍሮንቲዬ) ፍትህ የተደፈጣጠበት ውሳኔ ሲል ኮንኖታል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክሪስቶፍ ደሎይር ዛሬ በትዊተር ባወጡት መግለጫ

“ ውሳኔውን ተጠርጣሪዎቹን እስከመጨረሻው ድምጻቸውን ለማፈን የታለመ ነው ። ተጠርጣሪዎቹ እንዳይናገሩ በማድረግ ዕውነቱ በደምብ እንዲሸፋፈንላቸው ለማድረግ ነው ብለዋል።

ቱርክ የሳውዲውን የፍርድ ቤት ውሳኔ ከፍትህ የራቀ ስትል ኮንናዋለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG