በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዜጠኛው ዣማል ኻሾግዢ ጉዳይ ቱርክ ለሳዑዲ ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አደረገች


ጋዜጠኛው ዣማል ኻሾግዢ
ጋዜጠኛው ዣማል ኻሾግዢ

የሁለት ዜጋቿን እጆች አሳልፋ እንድትሰጣት ቱርክ ያቀረበችውን ጥያቄ ሳዑዲ አረቢያ ውድቅ አደረገች።

የሁለት ዜጋቿን እጆች አሳልፋ እንድትሰጣት ቱርክ ያቀረበችውን ጥያቄ ሳዑዲ አረቢያ ውድቅ አደረገች።

አንካራ የሳዑዲ አረቢያን የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የፈለገቻቸው ኢስታንቡል በሚገኘው የሪያድ ቆንስላ በጋዜጠኛው ዣማል ኻሾግዢ ላይ ጥቅምት ውስጥ ከተፈፀመው ግድያ ጋር በተያያዘ ነው።

የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብደል አል-ዡቤይር ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ “እኛ ዜጎቻችንን አሳልፈን አንሰጥም” ብለዋል።

አንድ የቱርክ ችሎት የአልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን ዋና ረዳትና የዙፋን ችሎች አማካሪ የነበሩት ሳዑድ አል-ቃሕታኒና የሃገሪቱ የደኅንነት የቀድሞ ኃላፊ አሕመድ አል-አሲሪ እንዲታሠሩ ወስኖ ባለፈው ሣምንት ውስጥ የመያዣ ዋራንት ቆርጧል።

ሁለቱ ሰዎች ግድያው የተፈፀመው የውንብድና አድራጎት ባካሄዱ ወኪሎች ነው ሲል የሳዑዲ መንግሥት ባሳወቀ ማግሥት ካባረራቸው የመንግሥቱ ባለሥልጣናት መካከል የሚገኙ ሲሆን በተለይ ቃሕታኒ የዩናይትድ ስቴትስም የገንዘብ ሚኒስቴር በግድያው ምክንያት ማዕቀብ ከጣለባቸው አሥራ ሰባት ሰዎች መካከል እንደሚገኙ ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG