በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳዑዲ አረቢያ የህዋ ፕሮግራም ልትጀምር ነው፣ ሴቶችንም ያሰለጥናል


ልዑል ሱልጣን ቢን ሳልማን
ልዑል ሱልጣን ቢን ሳልማን

ሳዑዲ አረቢያ ሴቶችን ጭምር የሚያሰለጥን የህዋ ፕሮግራም ልትጀምር እንደሆነ ትናንት ይፋ አድርጋለች።

በአልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን የሚደገፈው ፕሮግራም ሴቶች በሥራ መስክ በይበልጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አድርጓል።

“ሃገሪቱ የመጀመሪያዋን ሴት የሳዑዲ አረቢያ ዜጋ ወደ ህዋ በመላክ በታሪክ እንዲመዘገብ ታደርጋለች” ብለዋል የፕሮግራሙ ቃል አቀባይ።

እስላማዊቷ ሃገር "ራዕይ 2030" በሚለው ፕላኗ መሰረት የሳይንስና የቴክኖሎጂ ብልጽግና ፕሮግራም በማካሄድ ላይ ነች።

የአልጋ ወራሹ ግማሽ ወንድምና የአየር ኃይል አብራሪ የሆኑት ልዑል ሱልጣን ቢን ሳልማን በ1985 በተካሄደ የናሳ ዲስከቨሪ ሚሽን ውስጥ ከነበሩት ሰባት አባላት አንዱ ነበሩ።

ቢን ሳልማን የንጉሱ አማካሪ ሆነው ባለፈው ዓመት ከመሾማቸው በፊት፣ የሳዑዲ አረቢያ የህዋ ኮሚሽን ኃላፊ ሆነው ከእአአ 2018 ጀሞሮ አገልግለዋል።

XS
SM
MD
LG