በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሳዑዲ እስር ቤቶች “እየተሠቃየን ነን” ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግሥት እንዲመልሳቸው ተማፀኑ


በሳዑዲ እስር ቤቶች “እየተሠቃየን ነን” ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግሥት እንዲመልሳቸው ተማፀኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:57 0:00

በሳዑዲ እስር ቤቶች “እየተሠቃየን ነን” ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግሥት እንዲመልሳቸው ተማፀኑ

በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ በከፋ ሁኔታ ተይዘው እንደሚገኙ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ የገለጹ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ አገራቸው እንዲመልሳቸው ጠየቁ።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ፍላጎት እንዳለው የጠቀሱት ስደተኞቹ፣ በአንጻሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆነ፣ በሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ስለተባለው የታሳሪዎች ብዛት ከነጻ አካል ማረጋገጥ አልቻለም። በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነውም ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁንና፣ ከወራት በፊት በተመሳሳይ ጉዳይ ከአሜሪካ ድምፅ የተጠየቀው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከእስር የተፈቱ ስደተኞችን ለመመለስ እየሠራ እንደሚገኝ ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

ዘገባውን ያጠናቀረው የትግርኛ ክፍል ባልደረባ ገብረ ገብረ መድኅን ነው፤ ሀብታሙ ሥዩም ያቀርበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG