በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ዋሺንግተንን ይጎበኛሉ


የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን
የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን በዚህ ሳምንት ዋሺንግተንን ይጎበኛሉ።

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን በዚህ ሳምንት ዋሺንግተንን ይጎበኛሉ። ጉብኝቱን የሚያደርጉት የሃገራቸውና የኢራን ፉክክር እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት ነው።

ሞሃመድ ቢን ሳልማን ወደዩናይትድ ስቴትስ የሚመጡት የአዲስቱ ሳዑዲ አረብያ ራዕያቸውን ለማስተዋወቅ ሲሆን፣ ነገ ማክሰኞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሲያነጋግሩዋቸው፣ በደምብ እንደሚቀበሉዋቸው ይጠበቃል።

ሚስተር ትረምፕ የሱኒዎቹ ንጉሳዊ አስተዳደር ከሺያ መራሽዋ ኢራን ጋር ባላቸው ፉክክር በግልፅ ከነሱ ጎን መቆማቸው ሲታወስ፣ የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ይህን አጋጣሚ ሊጠቀሙበት የቸኮሉ ይመስላል።

አልጋ ወራሹ ለሲቢኤስ ቴሌቭዥን በሰጡት ቃል መጠይቅ የኢራኑን መሪ ከሂትለር ጋር ያወዳደሩ ሲሆን፣ ኢራን ኒውክሊየር መሳሪያ ከሰራች ሳዑዲም ፈጥና ትቀጥላለች ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG