በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሉጄይን አል- ሃትሉል ስድስት ዓመት ተፈረደባት


ፎቶ ፋይል፦ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሉጄይን አል- ሃትሉል 
ፎቶ ፋይል፦ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሉጄይን አል- ሃትሉል 

የሳዑዲ አረቢያ ፍርድ ቤት ታዋቂዋ የሴቶች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሉጄይን አል- ሃትሉል ላይ ዛሬ የስድስት ዓመት እስራት ፈረደባት።

ከአገሪቱ ብሔራዊ የዜና ምንጭች የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፤ በዛሬው ዕለት በሳዑዲ የተሰየመው የፀረ ሽብርተኛ ችሎት ባስተላለፈው ውሳኔ እ.አ.አ ከ2018 ጀምሮ ከሌሎች በደርዘን ከሚቆጠሩ የሴቶች የመብት ተሟጋቾች ጋር በእስር ላይ የምትገኘው ሉጄይን አል- ሃትሉል የኢንተርኔት መረብን በመጠቀም የውጭ ኃይሎችን አጀንዳ አራምዳለች በሚል ጥፋተኛ ብሏታል።

ሉጄይን አል- ሃትሉል ወንዶች በሴቶች ላይ እንዲተገብሩት በሕግ የተሰጣቸው የሞግዚትነት ሥልጣን እንዲነሳ እና ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ እንዲፈቀድ ስትወተውትና ስትታገል ቆይታለች። ትግል ስታካሂድ ከቆየችባቸው ነገሮች አንዱ መኪና ማሽከርከር የተፈቀደ ሲሆን እርሷ ግን በእስር ላይ ትገኛለች።

የሉጄይን ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ባለሞያዎች እና የዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ሕግ አውጭዎች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተቃውመውታል።

XS
SM
MD
LG