በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳውዲው ልዑል አልጋ ወራሽ “ጸረ-ሙስና” ዘመቻ እና ቀለመ ብዙ አንድምታዎቹ


ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ
ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ

“የሰላሳ ሁለት ዓመቱ ልዑል አልጋ ወራሽ ቢን ሳልማን እየወሰዳቸው ያሉት እርምጃዎች አንዳንዶች የአገሪቱን መሠረታዊ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ሕይወት ለመለወጥ የታሰበ እርምጃ አካል አድርገው ሲወስዱት ሌሎች ደግሞ ስልጣንን ጠቅልሎ ለመያዝ የሚያደርገው አድርገው ይመለከቱታል።” ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ የታሪክና ፖለቲካ መምሕር። “የቀድሞዎቹ የሳውዲ አረቢያ መሪዎች እያረጁ ነው። አዲሶቹ ደግሞ ሥልጣን እየፈለጉ ነው። ከዚያ አልፎ ግን የሳውዲ አረቢያን ንጉሳዊ አገዛዝ ይቀይራል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሌላው በየመን የያዙት ጦርነትና የተፈጠረው ውጥረት አለ። ይሄ በጣም አስጊ ነው።” ዶ/ር ዳንኤል ተፈራ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ ዋይት ዋተርስ የምጣኔ ሃብት ኢሜሪተስ ፕሮፌሰር።

ልዑላን፥ ሚንስትሮች እና ታዋቂ የንግድ ሰዎችን ጨምሮ ... የኢትዮጵያ ተወላጁ የሳውዲ ዜጋ ሼክ መሃመድ አል-አሙዲ አንዱ ናቸው .. ካለፈው ሳምንት መገባደጂያ አንስቶ እስካሁን ከሁለት መቶ በላይ የታወቁ ሰዎች የታሰሩበት የሳውዲው አልጋ ወራሽ የወሰዱት እርምጃ እያነጋገረ ነው።

የጠበቀ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በምትከተለውና ዘመንና አስተሳሰቦች ግብ-ግብ በገጠሙባት ሃገር ለውጥ አምጭዎቹ “አልመናል” የሚሉት መሠረታዊ የምጣኔ ሃብትና የባሕል ተሃድሶ በአንድ በኩል፤ የሥልጣን መንገዶች፥ የንዑስ አሕጉሩ የጸጥታ ጉዳዮችና የዓለም ገበያ በሌላው ጎራ ሆነው የተለየ ትኩረት ከሚሹበትና ወደ የት መሆኑ ገና የሚለይ ከሚመስለው ጎዳና እኩል የደረሱ ይመስላል።

Daniel Teferra
Daniel Teferra

የልዑል አልጋ ወራሹን መጠነ-ሠፊ እርምጃ ሁለንተናዊ አንድምታዎች የሚዳስስ የትንታኔ ውይይት ከታሪክ፥ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሃብት ጉዳዮች አዋቂዎች ጋር የሚደረግ ነው።

ተወያዮች:- ዶ/ር ዳንኤል ተፈራ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ ዋይት ዋተርስ የምጣኔ ሃብት መምሕር እና ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ በState University of New York at Stony Brook የአፍሪካ ዘመናዊ ታሪክና ፖለቲካ መምሕር ናቸው።

የሳውዲው ልዑል አልጋ ወራሽ “ጸረ-ሙስና” ዘመቻ እና ቀለመ ብዙ አንድምታዎቹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:55 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG