በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳዑዲ አረቢያ ለሴቶቿ ነፃነቶች "ቸረች"


የሳዑዲ አረቢያ ንጉሥ ሳልማን ለሃገራቸው ሴቶች ተጨማሪ መብቶች እንዲከበሩ ሰሞኑን ያስተላለፉት ውሣኔ ከአንዳንዶች ብዙ ሙገሣ እያተረፈላቸው ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ያለመደሰትና የወቀሣ ውርጅብኝም የሚያጎርፉባቸው አሉ፡፡

የሳዑዲ አረቢያ ንጉሥ ሳልማን ለሃገራቸው ሴቶች ተጨማሪ መብቶች እንዲከበሩ ሰሞኑን ያስተላለፉት ውሣኔ ከአንዳንዶች ብዙ ሙገሣ እያተረፈላቸው ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ያለመደሰትና የወቀሣ ውርጅብኝም የሚያጎርፉባቸው አሉ፡፡

ምንም እንኳ የሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ከንዑሣቸው አዳዲስ ነፃነቶች ቢቸሯቸውም አሁን ባሉበት አዲስ ሁኔታም ቢሆን ከሌሎች ብዙ ሃገሮች፤ በተለይ ደግሞ ከምዕራብ መሰሎቻቸው ጋር ፈፅሞ ሊተካከሉ አይችሉም፡፡

የሳዑዲ ቴሌቪዥን የግርማዊነታቸውን አዋጅ ባለፈው ሣምንት ያለ ብዙ አጀብና ያለ ጥሩንባ ጋጋታ ነው የተናገረው፡፡

የሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ከእንግዳህ ያለወንድ ፈቃድ ለከፍተኛ ትምህርት መመዝገብ ይችላሉ፤ ያለወንድ ይሁንታ የባንክ ሂሣብ መክፈት ይችላሉ፤ ታሥረው ከሆነ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ ለመውጣት በቅድሚያ ወንድ እንዲስማማ አይጠበቅም፡፡

ፓስፖርት መጠየቅ፣ ወደ ውጭ መጓዝ፣ ስለ ትዳር ማሰብ ግን ከወንድ ፍቃድ ውጭ ገና የማይታሰብ ነው በግርማዊነታቸው፤ በንጉሥ ሳልማን ሃገር፡፡

ርያድ ጥቂት ተጨማሪ ነፃነቶችን ለሴቶቿ የቸረችው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ጉዳዮች ኮሚሽን አባል በሆነች ማግሥት ነው፡፡ ይህ አባልነቷ ደግሞ የብዙ የመብቶች ተሟጋቾችን ቁጣ ቀስቅሷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ለሴቶቿ ነፃነቶች ቸረች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:45 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG