በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳዑዲ ዓረብያና ኪዩባ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መዝገብ ሰፈሩ


ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ
ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ

ሳዑዲ ዓረብያ እና ኪዩባ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን የመዋጋት ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ ሀገሮችን በሚዘረዝረው የዩናይትድ ስቴትስ መዝገብ ገብተዋል። ጉዳዩ ሃገሮቹን ይበልጡን ለማዕቀብ ያጋልጣቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት የዩናይት ስቴትስ ሸሪክ የሆነችው ሳዑዲ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን በተመለከተ የወነጀላት ሲሆን ኪዩባን ደግሞ ወደውጭ ሃገሮች ሃኪሞችን በምትልክበት መርኃ ግብሩዋ አማካይነት ህገ ወጥ የሰው ዝውውር ታካሂዳለች ሲል አውግዟታል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ህገ ወጥ የሰው ዝውውርን መታገላችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

ፕሬዚደንት ትረምፕ በአምናው ሪፖርት ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተፈረጁ ሃያ ሁለት ሃገሮች የሚሰጣቸው የተወሰነ ዓይነት ዕርዳታ እንዲገደብ ማዘዛቸውን ያስታወሱት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የዚያን ዕርምጃ መልዕክት ግልፅ ነው፤ ህገወጥ ዝውውርን ካልተጋፈጣችሁ ዩናይትድ ስቴትስ ትጋፈጣችኋለች ብለዋል።

በአሁኑ ሪፖርት ሦስተኛ ተርታ ውስጥ የገቡት ሳዑዲ እና ኪዩባ ቻይና ሰሜን ኮሪያና ሩስያን ተቀላቅለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG