በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን አንገት በመቅላት ገደለች


ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን አንገት በመቅላት ገደለች
ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን አንገት በመቅላት ገደለች

ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ሰሞኑን በሞት ቀጥታለች፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን አንገት በመቅላት ገደለች
ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን አንገት በመቅላት ገደለች

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:27 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ሰሞኑን በሞት ቀጥታለች፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ ታስረው የነበሩት ጂዛን በሚገኘው እሥር ቤት ውስጥ እንደነበረ ታውቋል፡፡

አረጋዊ ኃይለማርያም እና ሃዲሽ ዘላለም በሚባሉት ኢትዮጵያዊያን ላይ የሞት ቅጣቱ የተፈፀመባቸው አንገት በመቅላት መሆኑ ታውቋል፡፡

እዚያው ጂዛን እሥር ቤት ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እሥረኞች መካከል አንዱ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የተገደሉትን ሰዎች እንደሚያውቋቸውና ለአራት ዓመታት አብረው ታስረው መቆየታቸውን ገልፀው ሐምሌ 29/2007 ዓ.ም ከመካከላቸው ወስደው ቆራርጠውና አንገታቸውን ቀልተው እንደገደሏቸው ተናግረዋል፡፡

ሰዎቹ የተከሰሱት ከዚህ በፊት ከአንድ የሃገራቸው ሰው ጋር ድንገት ተጣልተው በተፈጠረ ነፍስ የማጥፋት ወንጀል እንደነበረ ታሣሪው ገልፀው የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት እንዲህ ዓይነቱን ሁኔታ ጠበቅ አድርጎ እንደማያጣራና የኢትዮጵያ መንግሥትም የዜጎቹን ሁኔታ በቅርብ እንደማይከታተል አመልክተዋል፡፡

ታስሮ የሚገኘው ሁሉ ወንጀለኛ ነው ወይስ አይደለም ብሎ የሚያጣራለት ማንም እንደሌለ ታሣሪው አመልክተዋል፡፡

ጂዛን እሥር ቤት ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን እሥረኞች እንደሚገኙና ብዙዎቹ ለዓመታት ያለክሥና ያለፍርድ ታጉረው እንደሚገኙ በየወቅቱ ሲናገሩ ይሰማል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ሰሞኑን አንገታቸውን በመቅላት ከገደለቻቸው ኢትዮጵያዊያን ጋር አንድ የራሷ የሳዑዲ አረቢያ ዜጋና አንድ ፓኪስታናዊ እንደሚገኙ ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡

አድራጎቱን በጥብቅ ያወገዘ አንድ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን “የሞት ዘመቻ” ሲል ጠርቶታል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ አደባባይ ላይ አንገት እየቀላች የገደለቻቸው ሰዎች ቁጥር ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ 114 መድረሱንና ባለፊው የአውሮፓዊያን 2014 ዓ.ም ሙሉውን ዓመት በተመሣሣይ ሁኔታ የተገደለው 87 ሰው እንደነበረ የፈረንሣይ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG