በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳኲናቪር ሃያ አምስት ዓመት ሆነው


ለኤችአይቪ/ኤድስ ሕክምና የዋለ አስተማማኝ መድኃኒት ሙከራ ከተጀመረ ዛሬ ሃያ አምስት ዓመቱን ደፈነ።

ኤችአይቪ በሃገሩ ተንሠራፍቶ ከሦስት መቶ ሺህ በላይ አሜሪካዊያንን ገድሏል። ጊዜው 1987 ዓ.ም. ነበር፤ ልክ የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት።

ከዚያ ቀደም ሲል አክት አፕ በሚል መጠሪያ የተደራጁ አሜሪካዊያን ለኤችአይቪ/ኤድስ ምርምርና ሕክምና ጠቀም ያለ ገንዘብ እንዲመደብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይወተውቱ ነበር።

የአክት አፕ መሥራች ሌሪ ክሬመር ባለፈው ዓመት ከማለፋቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ለቪኦኤ ሰጥተውት በነበረ ቃል ለኤድስ የተጋለጠው ማኅበረሰብ ጭራሽ ተዘንግቶና ተገፍቶም እንደነበር አስታውሰዋል። “ይህንን ያገኘውን ሁሉ የሚገድል ቫይረስ ለመዋጋት ዓለምን ለማንቃት ብቻችንን መጮህ ነበረብን” ብለዋል።

“ዝምታ ሞት ነው” በሚል መሪ ቃል ይንቀሳቀስ የነበረው የክሬመር ቡድን በዩናይትድ ስቴትስ ለመድኃኒቶች ዕውቅና የሚሰጠውን የምግብና የመድኃኒት አስተዳደርን ወረረ።

“ሙሉውን ሕንፃና ድርጅቱንም በወረራቸው መዝጋትና ማቆም በመቻላቸው አባነኑን” ብለዋል የአስተዳደሩ የኤችአይቪ/ኤድስ መርኃግብር የግንኙነት ዳይሬክተር ሪቻርድ ክላይን።

ሙሉውን ታሪክ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

ሳኲናቪር ሃያ አምስት ዓመት ሆነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:43 0:00


XS
SM
MD
LG