በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስምንት ቢሊዮን ዶላር አጭበርብሯል የተባለው የክሪፕቶ ከረነሲ መሥራች ሊፈረደበት ነው


ፎቶ ፋይል፦ ባንክማን ፍሪድ ማንሃተን ከሚገኘው ፌደራል ፍርድ ቤት፣ ኒው ዮርክ
ፎቶ ፋይል፦ ባንክማን ፍሪድ ማንሃተን ከሚገኘው ፌደራል ፍርድ ቤት፣ ኒው ዮርክ

ከደንበኞቹ ስምንት ቢሊዮን ዶላር አጭበርብሮ በመውሰድ ጥፋተኛ የተባለው የክሪፕቶ ከረነሲ ልውውጥ (FTX) መስራች ሳም ባንክማን ፍሪድ፣ ዛሬ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኒው ዮርክ ሲቲ የፌደራል ፍርድ ቤት የእስራት ቅጣቱን ይቀበላል ፡፡

ባንክማን ፍሪድ፣ ደንበኞች አሁን በኪሳራ ከተዘጋው የገንዘብ ልውውጥ FTX የተወስወደባቸውን አብዛኛውን ገንዘባቸውን መልሰው ያገኛሉ ሲል የተከራከረ ሲሆን ጠበቆቹም ቀለል ያለ እስራት እንዲቀጣ ጠይቀዋል፡፡

ባንክማን ፍሪድ ጥፋተኛ የተባለበትን ክስና ቅጣቱን አስመልክቶ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ይጠበቃል። የክሬፕቶ ከረነሲ የገንዘብ ልውውጥን ሲመራ ስህተት መስራቱን ያመነው ባንክማን ፍሪድ፣ የደንበኞችን ገንዘብ ለመስረቅ ግን ሆን ብሎ አለማሰቡን ተናግሯል፡፡

የ32 ዓመቱ ባንክማን-ፍሪድ፣ ሰባት የተለያዩ የማጭበርበር ክሶች የተመሰረቱበት ሲሆን በሰባቱም ጥፋተኛ ተብሏል። ድርጅቱን ለክስረት አጋልጧል የተባለው ባንክማን ፍሪድ፣ 8 ቢሊዮን ዶላር ከደንበኞቹ ከመውሰዱ ሌላ የድርጅቱን ባለሀብቶች 1.7 ቢሊዮን ዶላር አሳጥቷቸዋል፡፡

“በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ውስጥ ከታዩት ትልቅ የገንዘብ ማጭበርበር ክሶች ውስጥ አንዱ ነው” ሲሉ አቃቢያነ ህግ መናገራቸውን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG