“ሳልሳዊ ወያኔ ትግራይ” የተባለውና በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ፖለቲካ ፓርቲ ቅዳሜ ዕለት በመቀሌ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ለማካሄድ ያደረገው እንቅስቃሴ በፀጥታ ኃይሎች እንደታገደበት አስታወቀ።
በክልሉ ፓርቲዎች ሐሳባቸውን ለሕዝብ ለማድረስ እየተቸገሩ ነው ሲልም ፓርቲው ገልጿል።
የመቀሌ ከተማ ፀጥታና አስተዳደር በበኩሉ “ስለ ስብሰባው ጽሕፈት ቤታችን በጹሑፍ እንዲያውቀው ስላልተደረገ ነው የተከለከለው” ብሏል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።