በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በስለት በመወጋቱ ከፍተኛ ጥቃት የደረሰበት ሳልማን ሩሽዲ ሆስፒታል ገባ


Salman Rushdie Assault
Salman Rushdie Assault

ሳልማን ሩሽዲ በትላንትናው ዕለት ምእራብ ኒውዮርክ ውስጥ በተዘጋጀ አንድ ሥነ ስርአት ላይ ሊናገር ሲል በተሰነዘረበት ጥቃት ከባድ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ በዛሬው ዕለት ሆስፒታል ገባ።

የሩሽዲ ወኪል ሲናገሩ: የ75 ዓመት ዕድሜው ደራሲ “ጉበቱ ተጎድቷል፣ የእጅ ነርቮቹ ተቆርጠዋል፤ እናም ብርሃኑን ሊያሳጣው በሚችል አደጋ ዓይኑ ላይ ጉዳት ደርሶበታል። የሚተነፍሰውም በመሳሪያ እገዛ ነው።” ብሏል።

ሩሽዲ “ሰይጣናዊ ጥቅሶች” በሚል ርዕስ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1980ዎቹ የደረሰው ልቦለድ መድብል የኢራኑን መሪ የግድያ ዛቻ ማስከተሉ ይታወሳል። ሩሽዲ ላይ ጥቃቱን ያደረሰው ሰው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው የፌርቪው ኒውጀርሲ ነዋሪ የሆነው የ24 ዓመቱ ሃዲ ማታር መሆኑን ታውቋል። የማታር ጠበቃ ግን አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ፖሊስ በሩሽዲ ላይ ለደረሰው ጥቃት መንስኤው ምን ስለመሆኑ እስካሁን ግልፅ አይደለም ብሏል።

XS
SM
MD
LG