በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ ወደብ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የቻይናን ንግድ ይጎዳል


ፎቶ ፋይል፦ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የደረሰው ጉዳት፤ ደርባን ደቡብ፣ አፍሪካ እአአ ሚያዚያ 12/2022
ፎቶ ፋይል፦ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የደረሰው ጉዳት፤ ደርባን ደቡብ፣ አፍሪካ እአአ ሚያዚያ 12/2022

በደቡብ አፍሪካ የአገሪቱ ትልቅ ወደብ ላይ ጉዳት ያደረሰው የጎርፍ አደጋ አፍሪካ ወደ ቻይና የምታደርገው የውጭ ንግድ በተለይም እንደ ኮባልትና ሊቲየም ማዕድናትን ሊያስተጓጉል መቻሉን ባለሙያዎች አመለከቱ፡፡

የ400 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውና ወደ 40ሺ የሚደርሱ ሰዎችን ያፈናቀለው የጎርፍ አደጋን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በዚህ ሳምንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡ ከባዱ ፈተና በጎርፉ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የአገሪቱን ትልቁ ወደብ በድጋሚ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

“የደርባን ወደብ በአገሪቱ ትልቁና በአፍሪካ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚበዛበት የመርከቦች ማስተናጋጃ ነው ለአገራችን ኢኮኖሚ ወሳኝ ወሳኝ የሆነው ይህ ወደብ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡”

ወደ ወደቡ የሚያደርሰው መንገድ በቀን 13ሺ ከባድ ተሽከርካሪዎችን የሚያጓጉዝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 9ሺ የሚደርሱ ኮንቴነሮች በወደቡ መከማቸታቸው ተገልጿል፡፡ በዚህ ወደብ በደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስባት የደቡብ አፍሪካ ትልቋ የንግድ ሸሪክ የሆነችው ቻይና መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ቻይና ወደ አፍሪካ ከምትልካቸው ሸቀጦች 20 ከመቶ የሚሆነው የሚያልፈው በዚህ ወደብ በኩል ነው፡፡

XS
SM
MD
LG