በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካው ጎርፍ ጉዳተኞች በሌላ ከፍተኛ ዝናብ ተጠቁ


በደቡብ አፍሪካ የወደብ ከተማ ደርባን ቅዳሜና እሁድ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ መጠለያቸው መመታቱ ተገለጸ
በደቡብ አፍሪካ የወደብ ከተማ ደርባን ቅዳሜና እሁድ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ መጠለያቸው መመታቱ ተገለጸ

በደቡብ አፍሪካ የወደብ ከተማ ደርባን ባላፈው ወር በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ያጋገሙት ጉዳተኞች ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ መጠለያቸው መመታቱ ተነግሯል፡፡

ጉዳቱ የደረሰባቸውና ባለሙያዎች ለወደፊቱ ከእንዲህ ያለው ጉዳት የሚያድናቸው አዲስ የከተማ ንድፍና ግንባታ የሚያስፈልግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በታሪክ ከፍተኛ በሆነው ዝናብ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ወደ 7ሺ ሰዎች ቤት አልባ መሆናቸው ተነገሯል፡፡ የደቡብ አፍሪካ ፌዴራል መንግሥት አካባቢውን ለማጽዳትና መልሶ ለመገንባት 63 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን ምንም እርዳታ ያላገኙ መሆኑን የሚናገሩት ሰለባዎቹ ሁኔታዎች አሁንም ያልተሻሻሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG