በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ደቡብ ሱዳን የተሰደዱ ሱዳናውያን አሳሳቢ ችግር ገጥሟቸዋል


 በሀገራቸው የሚካሄደውን ጦርነት ሸሽተው ወደ ደቡብ ሱዳን የተሰደዱ ሱዳናውያን፣ ጁባ አቅራቢያ ከሚገኝ የደቡብ ሱዳን መጠለያ ጣቢያ እአአ ሰኔ 20/2023
በሀገራቸው የሚካሄደውን ጦርነት ሸሽተው ወደ ደቡብ ሱዳን የተሰደዱ ሱዳናውያን፣ ጁባ አቅራቢያ ከሚገኝ የደቡብ ሱዳን መጠለያ ጣቢያ እአአ ሰኔ 20/2023

በሀገራቸው የሚካሄደውን ጦርነት ሸሽተው ወደ ደቡብ ሱዳን የተሰደዱ 19ሺሕ ሱዳናውያን አሳሳቢ ችግር ገጥሟቸዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ ቁጥራቸው እጥፍ እንደሚሆን ግምቱን አስቀምጧል።

የሱዳኑ ጦርነት ባለፈው ሚያዚያ ከጀመረ ወዲህ፣ 100 ሺሕ የሚሆኑ ስደተኞች ደቡብ ሱዳን ገብተዋል፡፡አብዛኞቹ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ሲሆኑ፣ 19 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ሱዳናውያን ናቸው ተብሏል።

ስደተኞቹ በየግላቸው ከገጠማቸው ሰቆቃ በተጨማሪ፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን አለማወቃቸው አሳስቧቸዋል ሲል የቪኦኤው ሄንሪ ዊልኪንስ ከደቡብ ሱዳን በላከው ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG